text stringlengths 140 24k | summary stringlengths 13 164 |
|---|---|
አዲስ አበባ፣ ሀምሌ አምስት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በሁለት ሺህ በጀት አመት በአስቸኳይ የሙስና መከላከል ስራ ከሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊየን ብር በላይ ከሙስና እና ከምዝበራ ማዳን መቻሉን የፌደራል የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ ። በኮሚሽኑ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ገዛኸኝ ጋሻው በሁለት ሺህ በጀት አመት በተከናወኑ አበይት ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም በተጠናቀቀው በጀት አመት ከአንድ መቶ ሰባ አምስት ሺህ በላይ አመራርና ሰራተኞች ሀ... | በአስቸኳይ የሙስና መከላከል ስራ ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊየን ብር ከምዝበራ ማዳን ተቻለ |
አዲስ አበባ፣ መጋቢት ስድስት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡት ሶስት ትላልቅ የገበያ ማእከሎች በሙሉ አቅማቸው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አስታወቀ። አገልግሎት መስጠት የጀመሩት የኮልፌ እና ለሚ ኩራ የግብርና ምርቶች መሸጫ እንዲሁም የአቃቂ ቃሊቲ የሰብል ምርቶች መሸጫ ማእከላት መሆናቸው ተገልጿል። በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሰውነት አየለ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት ሀምሳ ሰባት አምራች እና አቅራ... | የመዲናዋ ሶስት የገበያ ማእከሎች በሙሉ አቅማቸው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው ተገለፀ |
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን ማክሰኞ ሌሊት ለረቡእ አጥቢያ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተፈፀመ ጥቃት ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኢሰመኮ እና አምንስቲ ኢንተርናሽናል ገለፁ።ጥፋተኞች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነውየግድያውን እውነተኛ መንስኤ የሚያጣራ ኮሚቴ ይቋቋምቢቢሲ በተጨማሪ በጥቃቱ አካባቢ የነበሩ የአይን እማኞችንና በአካባቢው በሚገኝ ሆስፒታል የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎችን በማናገር ለመረዳት እንደቻለው አንድ መቶ ሀያ ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች በርካቶች ደግሞ ከባ... | ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን በተፈፀመው ጥቃት ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች መገደላቸውን የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ገለፁ |
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት ስድስት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ኢትዮ ቴሌኮም በተያዘው በጀት አመት በመጀመሪያው ሩብ አመት አስር ነጥብ አንድ ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ።የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ የኩባንያውን የመጀመሪያ ሩብ አመት ስራ አፈፃፀም በተመለከተ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥተዋል።ወይዘሪት ፍሬህይወት በመግለጫቸው ኢትዮ ቴሌኮም በተያዘው በጀት አመት መጀመሪያ ሩብ አመት ላይ የተለያዩ የአሰራር ማሻሻያዎች ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል።ተቋሙ የእቅዱን ዘጠና ስም... | ኢትዮ ቴሌኮም በመጀመሪያው ሩብ አመት አስር ነጥብ አንድ ቢሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ |
ነገረ ኢትዮጵያ ገዥው ፓርቲ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን ለማሰር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የነገረ ኢትዮጵያ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ሰሞኑን የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ባደረጉት ስብሰባ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃልን ወይንስ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችን ማሰር ያዋጣል በሚል ልዩነት እንደተፈጠረ የገለፁት ምንጮቻችን በስተመጨረሻም የኢንጅነር ይልቃል መታሰር ትኩረት የሚስብ በመሆኑ ንቁ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችን ማሰር አዋጭ ነው የሚለው ቡድን ተደማጭነት እንዳገኘ ለነገረ... | ኢህአዴግ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ለማሰር መዘጋጀቱ ታወቀ የኢህአዴግ አመራሮች መካከል ልዩነት ተፈጥሯል |
በአዲስ አበባ ከተማ በ ሚሊዮን ብር ወጪ የተገዙ ሀምሳ አራት የደረቅ ቆሻሻ አንሺ መኪኖች ለበርካታ ወራት ወደ ስራ ሳይገቡ መቆየታቸው ተገለፀ ።በአዲስ አበባ እሳት እና ድንገተኛ አደጋ መከላከልና መቆጣጠሪያ ባለስልጣን ግቢ እና ሌሎች ቦታዎች ቆመው የቆዩ እነዚህ መኪኖች በአዲስ አበባ ፅዳት አስተዳደር ስር የተደራጁ የደረቅ ቆሻሻ አንሺ ማህበራት ለስራቸው እንዲገዛ ያዘዛቸውና በሚፈልጉበት ደረጃ ባለመገዛታቸው ነው የተባለው።ስላሳ አምስት ኩንታል የሚጭን የደረቅ ቆሻሻ ማንሻ መኪኖች እንዲገዛ ያዘዙት እነዚህ... | ሀምሳ አራት የደረቅ ቆሻሻ አንሺ መኪኖች ለበርካታ ወራት ወደ ስራ ሳይገቡ መቆየታቸው ተገለፀ |
የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማሀበር አይኤኤኤፍ በወርቅ ደረጃ ከሚመድባቸው የጎዳና ውድድሮች የለንደን ማራቶን ተጠቃሽ ነው። ከተመሰረተ አራት አሰርታት ያስቆጠረው ለንደን ማራቶን እንግሊዛውያን ከማንነታቸው ጋር የሚያይዟቸውን ታሪካዊ ቅርሶቻቸውን ለአለም ህዝብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚያስተዋውቁበት መድረክ እንደሆነ ይታመናል። ውድድሩ ባለፈው እሁድ ሲካሄድ ኬንያዊ ኤሊዩድ በአሸናፊነት ሲያጠናቅቅ፣ ሙስነት ገረመው ሁለተኛ በመሆን አጠናቋል። ሙሌ ዋሲሁን ሶስተኛ የነሀስ ሜዳሊያ ባለቤት ሆኗል። በሴ... | ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ተስፋ የተጣለበት ሙስነት ገረመው |
የሰብአዊ መብት ጥሰት ተጠርጣሪዎች ተቋማትም ተጠያቂ መሆን አለባቸው አሉየፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን በብሄራዊ መረጃና ደሀንነት አገልግሎት ውስጥ አደገኛ መርዝ ማግኘቱን አስታወቀ። የመርዙን አይነትና የጉዳት መጠን በባለሙያ ለማስመርመር እየሰራ መሆኑን በመግለፅ፣ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ እንደሚያስፈልገውም ገልጿል። መርማሪ ቡድኑን በመቃወም ተጠርጣሪዎች ለፍርድ ቤቱ በተቋሙ ውስጥ መርዝ እንዳለ የተናገሩት እነሱ መሆናቸውን አስረድተው፣ ይኼንንም ያደረጉት መርዙ አደገኛ በመሆኑ ዜጎች ሳያውቁ ቢነኩት ከ... | በብሄራዊ መረጃና ደሀንነት አገልግሎት ውስጥ አደገኛ መርዝ መገኘቱን የፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ |
በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ዘይድ ራአድ አል ሁሴን ከሚያዝያ ሀያ አራት ሀያ ስድስት ሁለት ሺህ ዘጠኝ አመተ ምህረት ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ።ኮሚሽነሩ የኢፌዴሪ መንግስት ባደረገላቸው ግብዣ መሰረት ነው ሀገሪቱን የሚጎበኙት።እግረ መንገዳቸውን ከአፍሪካ ህብረት መሪዎች ጋር እንደሚወያዩም ታውቋል።በኢትዮጵያ ቆይታቸው የሀገሪቱን የሰብአዊ መብት ሁኔታና የመንግስታቱን ድርጅት የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ተግባራት በተመለከተ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ... | በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው |
ላለፉት አመታት ከተለያዩ የአለም አገራት የባኞ ቤት የህንፃ ማጠናቀቂያ የሳውና የጃኩዚና መሰል የሴራሚክ ምርቶችን በማስመጣት ለአገር ውስጥ ገበያ ሲያቀርብ የቆየው ኢትዮ ሴራሚክስ አምስተኛውን ትልቅና ዘመናዊ የሴራሚክስ መሸጫ ማእከል ቦሌ ኖቪስ ሱፐር ማርኬት ፊት ለፊት አዲስ በገነባው ህንፃ ላይ ከፈተ። ከትላንት በስቲያ በይፋ ስራ የጀመረው ይሄው መደብር ከሌሎቹ መደብሮች በተለየ የተደራጀና እቃዎች ተገጣጥመው ዲስፕሌይ የተደረጉበት ሲሆን ማንኛውም ደንበኛ እቃዎቹን ሲገዛ ምን እንደሚመስሉና ምን ቅርፅ እን... | ኢትዮ ሴራሚክስ ኛውን ትልቅና ዘመናዊ ሾውሩም በቦሌ ከፈተ |
መጋቢት ፳ ሀያ ቀን ፳፻፰ አመተ ምህረት ኢሳት ዜና በደቡብ ክልል ሰሜናዊ ዞን በሀላባ ማረቆ ወረዳ የተከሰተው መጠነ ሰፊ የርሀብ አደጋ አስከፊ መሆኑን ዩኒሴፍ አስታውቀዋል። በደቡብ ክልል ከሚገኙ አንድ መቶ ስላሳ ስድስት የገጠር ወረዳዎች ውስጥ በክልሉ ትርፍ አምራች የነበሩት ሰባ ሶስት ወረዳዎች ከፍተኛ አደጋ ይንዣበባቸው ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ አርባ አምስትቱ ወረዳዎች በዝናብ እጥረት ምክንያት አስጊ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ዩኒሴፍ አመልክቶአል። ድርቁን ተከትሎ የተፈጠረው የውሀ እጥረት እንስሳት ላይ... | በደቡብ ክልል ማረቆ ወረዳ በእርሀቡ ምክንያት ታዳጊ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደዱ |
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ ስምንት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ እነ አቶ እስክንድር ነጋ በተጠረጠሩበት የእርስ በርስና የሀይማኖት ግጭት ማስነሳት ወንጀል አራት ምስክሮችን ችሎት አቅርቦ አሰምቷል።በዚህም ሶስትኛ፣ አምስትኛ፣ ስድስትኛ እና ሰባትኛ ተራ ቁጥር ላይ የተመዘገቡ ምስክሮች ቀርበው ቃላቸውን ሰጥተዋል።እነ አቶ እስክንድር በነሀሴ ስድስት ቀን ጠበቆቻችንን አንፈልግም ብለው ማሰናበታቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ህገ መንግስታዊ መብታቸው እንዲጠበቅ የመንግስት ተከላካይ ጠበቃ ያቆመላቸውና ... | አቃቤ ህግ በእነ አቶ እስክንድር ነጋ ላይ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን አሰማ |
ኔልሰን ማንዴላ የደቡብ አፍሪካ የፀረአፓርታይድ የዘርመድሎ ተዋጊ አርበኛ መሆናቸው ይታወቃል። በደቡብ አፍሪካ ዘረኛ መንግስትለእስር የተዳረጉት ኢትዮጵያ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና ወስደው እንደተመለሱ ነበር። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ አም ማንዴላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ኢትዮጵያ ፓስፖርት በመስጠት አጋርነቷን የገለፀች ብቸኛ ሀገር ነበረች።ከዘመናት በሀላ ማንዴላ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ወቅት የግድያ ሙከራ ሴራ ተደርጎ እንደነበር ሚስጥሩን ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ ይዘው የቆዩ በቀዳማዊ አፄ ሀይለስላሴ ዘመን ... | ማንዴላን በተመለከት ለግማሽ አመታት የተደበቅ ምስጢር |
ባሌ ሮቤ፦ የሰብል ማጨጂያና መውቂያ ማሽን ኮምባይነር እጥረት ምርትን በወቅቱ ለመሰብሰብ ስጋት እንደፈጠረባቸው በኦሮሚያ ክልል የባሌ ዞን አርሶ አደሮች ገለፁ። የባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ አርሶ አደሮች ሰሞኑን ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ በአካባቢያቸው በኮምባይነር ሰብልን ማጨድና መውቃት የተለመደ ነው። ይሁን እንጂ በዘንድሮ የምርት ዘመን የኮምባይነር አቅርቦት እጥረት በማጋጠሙ ምርታቸውን በወቅቱ ሰብስበው ለማስገባት ስጋት ፈጥሮባቸዋል። የኮምባይነር ተጠቃሚ ከሆኑት አንዱ አርሶ አደር አብዱል ሀኪም ... | የሰብል ማጨጂያና መውቂያ ማሽንእጥረት ስጋት ፈጥሯል |
ፀረ አረም መድሀኒቶችን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ አቅዷልበፕራይቬታይዜሽንና የመንግስት የልማት ድርጅት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ከሚያስተዳድራቸውና ለሽያጭ አቅርቧቸው ከነበሩ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ውስጥ አንዱ የሆነው አዳሚ ቱሉ ፀረ ተባይ ማዘጋጃ አክሲዮን ማህበር ከ ሚሊዮን ብር በላይ ያስገነባውን አዲስ ማምረቻ በማጠናቀቅ ስራ ጀመረ።ከአዲስ አበባ በ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዝዋይ ከተማ የተገነባውና ስራ የጀመረው ማምረቻ የተባለውን ፀረ አረም መድሀኒት የሚያመርትና በተለያዩ መጠን ባላቸው መያዥያዎች ... | አዳሚ ቱሉ አዲሱን ፀረ አረም ማምረቻውን ስራ አስጀመረ |
በስደት ምክንያት ከኢትዮጵያ ወጥተው በሳኡዲ አረቢያ፣ በግብፅና በሊባኖስ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን፣ ከፍተኛ የአካል ጉዳት እየደረሰባቸው በግድ እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑ ታወቀ።ከሳኡዲ አረቢያ ተመላሾች የአቀባበልና አሸኛኘት ኮሚቴ አባልና የብሄራዊ የአደጋ መከላከልና ስጋት አመራር ኮሚሽን ተወካይ አቶ አስመላሽ ገብረ ህይወት ሀሙስ ሀምሌ ሀያ ቀን ሁለት ሺህ ዘጠኝ አመተ ምህረት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፣ ከሰኔ ሀያ ስድስት እስከ ሀምሌ ሀያ ቀን ሁለት ሺህ ዘጠኝ አመተ ምህረት ብቻ ... | በርካታ ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረቢያና ከግብፅ በግዳጅ እንዲወጡ እየተደረገ ነው |
አዲስ አበባ፣ ሀምሌ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በደቡብ ክልል ባለፈው በጀት አመት ከማእድን ልማት ዘርፍ ከአንድ መቶ ሀያ አምስት ነጥብ ሁለት ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለፀ። በክልሉ በማእድን ልማት የተሰማሩ ባለሀብቶች ከ ሺህ በላይ ለሆኑ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠራቸውም ተመላክቷል። የክልሉ የማእድን ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ አፀደ አይዛ በክልሉ ለኢንዱስትሪ ግብአት አንድ መቶ ሀያ አምስት ሺህ አራት መቶ አርባ ቶን ማእድናትን ማምረት መቻሉን ተናግረዋል። ከተመረተው ማእድን አንድ... | በደቡብ ክልል ከማእድን ልማት ዘርፍ ከአንድ መቶ ሀያ አምስት ነጥብ ሁለት ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለፀ |
አዲስ አበባ፣ መጋቢት ሶስት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ስኬት የወጣቶችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ሲሉ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር ገለፁ። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የወጣቶች የሰላም ጉባኤ ማጠናቀቂያ መርሀ ግብር በዛሬው እለት ተካሂዷል። በመድረኩ የተገኙት ከንቲባ ከድር ጁሀር በሰላም እሴት ግንባታ ጉልህ ሚና የሚጫወቱ ሚዛናዊ ወጣቶችን ማፍራትና ማብቃት ይኖርብናል ብለዋል። ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህ... | ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ እድገት የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማሳደግ ከፍተኛ ሚና አለው ከንቲባ ከድር ጁሀር |
የህዋ ተመራማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የብላክ ሆል ምስልን በጣም ሩቅ ካለ የክዋክብት ስብስብ ውስጥ ማንሳት ችለዋል። አርባ ቢሊየን ኪሎሜትር ይረዝማል የተባለው ብላክ ሆል ምድርን በሶስት ሚሊየን እጥፍ ይበልጣታል ተብሏል። የዘርፉ ባለሙያዎች ትልቅ አውሬ የሚል ስያሜ ሰጥተውታል። ይህንን አስገራሚ የብላክ ሆል ምስል ለማንሳት አገልግሎት ላይ የዋሉትን ስምንት ቴሌስኮፖች በማጣመር አንድ ወጥ ምስል እንዲገኝ ያደረገችው ደግሞ የሀያ ዘጠኝ አመቷ ሳይንቲስቷ ኬቲ ቦውማን ነች። ጨረቃን የሚረግጠው የመጀመሪያው ጎብኚ ... | ከመጀመሪያው የብላክ ሆል ምስል ጀርባ ያለችው ሴት |
ስልሳ ሰባት በዛብህ መለዮ ሰማኒያ አንድ አብዱልከሪም መሀመድተጠናቀቀ ጨዋታው አንድ አንድ በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል።ተጨማሪ ደቂቃ ሶስትየተጫዋች ለውጥ ድቻአማኑኤል ተሾመ ወጥቶ ዮሴፍ ድነንገቱ ገብቷል።ጎልልል ቡናሰማኒያ አንድ ኤልያስ ማሞ ያሻማውን ኳስ አብዱልከሪም መሀመድ በግንባሩ በመግጨት ቡናን አቻ አድርጓል።የተጫዋች ለውጥ ድቻበዛብህ መለዮ ወጥቶ ዳግም በቀለ ገብቷል።ጎልልል ድቻ ስልሳ ሰባት በዛብህ መለዮ በግሩም ቅብብል ግብ አስቆጥሮ ድቻን ቀዳሚ አድርጓል። ሀምሳ አምስት ከመጀመርያው አጋማሽ በተሻ... | ወላይታ ድቻ ከ ኢትዮጵያ ቡና ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት |
የወሰን ማካለሉ ስራ በሁለት ወራት ውስጥ የተከናወነ ሲሆን በሁለቱ ክልሎች መካከል ቀሪ ስልሳ ሶስት ቀበሌዎችን የማካለሉ ስራም እየተሰራ ነው ተብሏል።የሁለቱ ክልሎች ርእሳነ መስተዳደሮች ሚያዚያ ሀያ ስምንት ሁለት ሺህ ዘጠኝ የድንበር ማካለሉን ስራ በሶስት ወራት ውስጥ ለማከናወን ስምምነት ፈፅመው እንደነበር ይታወሳል።በስምምነቱ መሰረት ከዚህ ቀደም ሳይከለሉ የቀሩትን ጨምሮ በምእራብ እና ምስራቅ ሀረርጌ፣ ባሌ፣ ጉጂ እና ቦረና ዞኖች በሀያ አራት ወረዳዎች የሚገኙ አንድ መቶ አርባ ስምንት ቀበሌዎች መካለል ... | በኦሮሚያና ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች ሰማኒያ አምስት አጎራባች ቀበሌዎችን ወሰን የማካለል ስራ ተሰራ |
አዲስ አበባ፣ መስከረም ሰባት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ከ ሶስት ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ መሰማራታቸው ተገለፀ።እየተካሄደ ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግም በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል።የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍቅሬ አማን እንደገለፁት በዞኑ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት በተደረገ ጥረት ከ ሶስት ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች በግ... | በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ከ ሶስት ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ መሰማራታቸው ተገለፀ |
አዲስ አበባ፣ ግንቦት ሰባት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት የጋራ መርህ ላይ ተመስርተው ጠንካራ ተቋም እንዲፈጥሩ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ አሳሰቡ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፣ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እና ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የእምነት መሪዎች ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የጋራ እሴቶችን በመጠቀም ፈጣሪን ... | ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት የጋራ መርህ ላይ ተመስርተው ጠንካራ ተቋም እንዲፈጥሩ አሳሰቡ |
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የዋጋቸውን እጥፍ የሚሆን የተጠየቀባቸውን ሀያ ተሽከርካሪዎች ታክስና ቀረጥ ከፍሎ ለመረከብ፣ የባለስልጣኑ የተለያዩ ከፍተኛ ሀላፊዎች እየተወዛገቡ መሆኑን ታወቀ። አውቶሞቢሎቹን ቶዮታ ያሪስ ለማቅረብ በወጣው ጨረታ ከተሳተፉት ተሽከርካሪ አቅራቢ ድርጅቶች መካከል፣ በላይ አብ ሞተርስና ሞኤንኮ የሞተርና ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማሀበር በባስልጣኑ የቀረበውን መስፈርት በማሟላት የመጨረሻዎቹ ተወዳዳሪዎች እንደነበሩ ሰነዶቹ ያሳያሉ። በላይ አብ ሞተርስ ሀያ ቶዮታ ያሪስ አውቶሞ... | የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ሀላፊዎች በተሽከርካሪዎች ግዥ እየተወዛገቡ ነው |
አቶ መላኩ ፋንታ እና አቶ ገዋህድ ወጊዮርጊስ በ መዝገቦች ተከሰዋልሶስት ተጠርጣሪዎች በነፃ ተለቀዋልየፌደራሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ ከ በላይ በሚሆኑ የገቢዎችና ጉምሩክ መስሪያ ቤት ባለስልጣናት እና የቅርንጫፉ ፅህፈት ቤት ሰራተኞች እንዲሁም ከባለስልጣናቱና ሰራተኞች ጋር ተመሳጥረው ከባድ የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በተባሉት ባለሀብቶች ላይ የክስ መዝገቦች አደራጅቶ ከፈተ። በምርመራ ቀጠሮ ላይ የቆዩ ተጠርጣሪዎች በነፃ ሲለቀቁ ቀደም ሲል በዋለው ችሎት ምርመራቸው አልተጠናቀቀም ተብለው... | በገቢዎችና ጉምሩክ ተጠርጣሪዎች ላይ የክስ መዝገቦች ተከፈቱ |
ለክቡር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጉዳዩ፡ በኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀፅ ስላሳ ሰባት አንድ መሰረት ፍትህ ለማግኘት ለሁለተኛ ጊዜ የቀረበ አቤቱታ፤ አንድ በኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀፅ ሀምሳ አንድ አንድ ህገ መንግስቱን መጠበቅና መከላከል የፌዴራል መንግስት ስልጣንና ተግባር በመሆኑ፤ ሁለት በኢፌዲሪ ህገ መንግስት አንቀፅ ሰባ አራት ህገ መንግስቱን ማክበርና ማስከበር የጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣንና ተግባር በመሆኑ፤ አቤቱታዬን እነሆ ለሁለተኛ ጊዜ ለክቡርነትዎ ለማቅረብ ተገድጃለሁ... | ይድረስ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ህገ መንገስቱ ተጣሰ፣ ሻለቃ መላኩ ተፈራ ታገተ |
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት አስር ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በኢትዮጵያ አሁን ላይ በኮቪድ ከሚያዙ ሰዎች ውስጥ ነጥብ ዘጠኝ በመቶዎቹ ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል እንደሚገቡ ተገለፀ። በኢትዮጵያ የኮቪድ ስርጭት ያለበት ሁኔታ እና ከመነሻው ጀምሮ እስካሁን ን ምላሽ በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሀን ገለፃ ተደርጓል። የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አስቻለው አባይነህ እንዳሉት ኮቪድ በአለም ጤና ድርጅት የአለም የጤና ስጋት መሆኑንና ሀገራት ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ከመገለፁ አስቀድሞ ... | በኢትዮጵያ በኮቪድ ከሚያዙ ሰዎች ውስጥ በመቶ የሚሆኑት ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል ይገባሉ |
ህዳር ቀን አመተ ምህረት ከቀትር በኋላ በ ሲኖትራክ ተሽከርካሪዎች ግምቱ ከ ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ ለ ቤቶች ግንባታ የሚውል የአርማታ ብረት ዘርፈዋል ተብለው የታሰሩ ሰባት ግለሰቦች ላይ ክስ ተመሰረተባቸው።የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ታህሳስ ቀን አመተ ምህረት ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው ክስ እንደሚያስረዳው ተከሳሾቹ የዝርፊያ ወንጀሉን የፈፀሙት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ መጋዘን ነው። መጋዘኑ የሚገኘው በንፋስ ስልክ ላፍቶ... | ከ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የ ቤቶችን ብረት ዘርፈዋል የተባሉ ክስ ተመሰረተባቸው |
ጀማል ባለፈው ማክሰኞ በቱርክ ኢንስታንቡል የሳኡዲ ቆንስላ ቀጠሮ ነበረው። የጋብቻ ጉዳዮችን ለመጨራረስ፤ የቀድሞው ባለቤቱን የፍቺ ጉዳይ ለመዝጋት አዲሷን ቱርካዊት ባለቤቱን አስከትሎ ወደዚያ ሄደ። ደጅ ጠብቂኝ መጣሁ አላት። በዚያው አልተመለሰም። የመጀመርያው ጥርጣሬ ሳኡዲ አፍና ወደ አገሯ ልካዋለች የሚል ነበር። አሁን እየወጡ ያሉ መረጃዎች ግን እዚያው ቆንስላው ውስጥ በምስጢር እንደተገደለ ፍንጭ የሚሰጡ ናቸው። የማትተነፍሰው ከተማ አዲስ አበባ የጠፉት የኢንተርፖል ሹም ቻይና ውስጥ ተገኙ ሳኡዲያዊው ጀማ... | በገዛ አገሩ ኤምባሲ ውስጥ የተገደለው ጋዜጠኛ |
አዲስ አበባ፣ ሀምሌ አስር፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ሰራተኞች ዛሬ እየተከናወነ በሚገኘው በአንድ ጀንበር አምስት መቶ ሚሊዪንችግኝ የመትከል መርሀ ግብር ላይ ተሳተፉ። በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በትዊተር ገፁ የአየር ንብረት ለውጥ ድንበር እንደማይገድበው ሁሉ የአረንጓዴ አሻራም ወሰን የለውም ብሏል። ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ በአረንጓዴ ልማት ዘርፍ በጋራ እየሰሩ መሆኑን የጠቆመው ኤምባሲው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን... | በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች በአንድ ጀንበር አምስት መቶ ሚሊዪን ችግኝ የመትከል መርሀ ግብር ላይ ተሳተፉ |
የጥቃቅንና አነስተኛ አሰሪዎች ፌዴሬሽን ራሱን ችሎ በፌዴሬሽን ደረጃ የተቋቋመው አምና ሁለት ሺህ ዘጠኝ አመተ ምህረት ነበር። በመላው አገሪቱ በጥቃቅን፣ ታዳጊና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በተደራጁ ሁለት ሺህ ማሀበራት አማካይነት የተመሰረተ ነው። ራሱን ችሎ የተቋቋመበት ምክንያት ኢንተርፕራይዞችን የሚወክሉ ማሀበራት በመበራከታቸውና በስራቸው የሚያቅፏቸው ሰራተኞችም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ በመምጣታቸው የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ሰላማዊ ለማድረግ ከወዲሁ ማሀበራትን ወደ ፌዴሬሽን ደረጃ ማሳደግ አስፈላጊ በመሆ... | ባንክ ለማቋቋም የሰነቀው የጥቃቅንና አነስተኛ አሰሪዎች ፌዴሬሽን |
ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ ከጋዜጠኛ መአዛ ብሩ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ አዳመጥኩት።ግሩም ነበርጋዜጠኛዋ ወይዘሮ መአዛ ብሩ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች እንደተለመደው በሳል እና ሰፋ አድርጎ ለመናገር የሚመቹ እና የሚጋብዙ ነበሩ።ከጠቅላይ ሚኒስተርው ተፈጥሮ የምወድላቸው ለህዝብ ቀረብ የማለት ሰዋዊነት ለጠያቂ ጋዜጠኛም ምቾት መስጠቱ አይቀርም።መደብ ላይ እየተኛሁኩራዝ የሚበራበት ቤት ውስጥ ያደግኩ ነኝ ሲሉ አድማጭ ከእኛ እንደ አንዱ እንጅ ከሰማይ ዱብ ብለው ዙፋን ላይ ያረፉ አለመሆናውን ይረዳልይህ አይነቱ ሰው ሰ... | ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ ከጋዜጠኛ መአዛ ብሩ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ መስከረም አበራ |
በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት የተፈጠረውን መጨናነቅ ለመቀነስ፣ መደበኛ ያልሆነ የበረራ አገልግሎት ለሚሰጡ የግል አየር መንገዶች ብቻ የሚያገለግል ኤርፖርት ለመገንባት ጥናት እየተካሄደ እንደሆነ ተጠቆመ። የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንና የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት በጋራ ከባለድርሻ አካላት ጋር የካቲት ሀያ ስድስት ቀን ሁለት ሺህ ሰባት አመተ ምህረት ባካሄዱት ስብሰባ፣ መንግስት በአዲስ አበባ አነስተኛ አውሮፕላኖች የሚስተናገዱበት የተለየ ኤርፖርት እንዲገነባ የግል አየር መንገዶች በተደ... | ለግል አየር መንገዶች የሚያገለግል ኤርፖርት ለመገንባት ታስቧል |
አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ ሀያ አምስት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ባለፉት ሀያ አራት ሰአታት ውስጥ በተደረገ ሺህ ሶስት መቶ ስልሳ አራት የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ አንድ ሺህ ዘጠኝ ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ ። ሚኒስቴሩ በእለታዊ መግለጫው በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሀምሳ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ስላሳ አንድ ደርሷል። በሌላ በኩል ስድስት መቶ ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አራት ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።... | ባለፉት ሀያ አራት ሰአታት አንድ ሺህ ዘጠኝ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ ሰዎች ህይወት አልፏል |
ኢሳት ነሀሴ አራት ሁለት ሺህ ስምንት የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በሳምንቱ መገባደጃ በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የተፈፀሙ ግድያዎችን በገለልተኛ አለም አቀፍ ታዛቢ ቡድን ማጣራት እንዲደረግበት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ውይይት በማካሄድ ላይ መሆኑን ረቡእ ይፋ አደረገ። በአለም ዙሪያ የሚፈፀመው የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የሚከታተለው ይኸው አካል የኢትዮጵያ መንግስት ከአለም አቀፍ ገለልተኛ አካል በሯን ክፍት እንድታደርግ በይፋ መጠየቁን ሮይተርስ ከጄኔቭ ዘግቧል። ከቀናት በፊት ከአንድ መቶ ለ... | የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የተፈፀሙ ግድያዎችን በገለልተኛ አለም አቀፍ ታዛቢ ቡድን ማጣራት እንዲደረግበት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እየተወያየ እንደሆነ ገለፀ |
አዲስ አበባ፣ ሰኔ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የዚምባብዌ የፀረ ሙስና ኮሚሽን በሀገሪቱ ሀብታሞች የገንዘብ ምንጭ ላይ ምርመራ ጀመረ። ምርመራው በሀገሪቱ ባለ ፀጎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ የሀብት ምንጫቸውን ማጣራትና እነርሱ የሚያንቀሳቅሱት ድርጅት ግብር መክፈል አለመክፈሉን የሚያካትት መሆኑን የፀረ ሙስና ኮሚሽነሩ ማታንዳ ሞዮ ተናግረዋል። በዚህ ሂደት መሰረትም ባለ ፀጎቹ የሀብት ምንጫቸውን በሀገሪቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው አሳማኝ በሆነ መልኩ ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል ነው ያሉት። ይህ ሳይሆን ቢቀ... | ዚምባብዌ በሀገሪቱ ሀብታሞች የገንዘብ ምንጭ ላይ ምርመራ ጀመረች |
በሳውዲ ንጉስ ጥብቅ ትእዛዝ በተጀመረው የፀረሙስና ማፅዳት ዘመቻ ሽህ መሀመድ ሁሴን አልአሙዲ መታሰራ ቸውን ከሳውዲ መንግስት በወጣ መረጃ አላረጋገጥኩም ። መታሰራቸው ግን በተለያዩ ታዋቂ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀንን ጨምሮ የአረብ መገናኛ ብዙሀን ዜናውን በሰፊው በዝርዝር እየተዘቡት ነው በሪያድ የጀርመን ራዲዮ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ስለሽ ሽብሩ ምንጩን ባይጠቅስም የሸሁን በሪያድ መታሰር አረጋግጧል ።እንደኔ እንደኔ መረጃዎችን ቀስ ብሎ ማጣራትና ማረጋገጥ ይገባል። ይህ መሰሉን ከፍተኛ የፀረ ሙስና እስር በሚመለከ... | የመረጃ ግብአት በሸህ አልአሙዲን እስር ዙሪያ ነቢዩ ሲራክ |
የመንግስት ባለስልጣናትን ሀብት በመጪው መስከረም ወር ለህዝብ በይፋ እንደሚያሳውቅ የፌደራል ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ናስታወቀ።የፌደራል ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ እዬልኝ ሙሉ አለም እንደገለፁት የኮሚሽኑ ተግባር ሀብትን መመዝገብ ብቻ ሳይሆን ፣ ሹመኛው ወይም ሰራተኛው ያስመዘገበው ሀብት ትክክል ነው ወይስ አይደለም የሚለው መረጋገጥ ጭምር እንደሆነ በመጥቀስ፤ መዝግቦ እና ማጣራት አድርጎ ያረጋጠውን ሀብት ለህዝቡ በግልፅ ይፋ ማድረግ በአዋጅ የተደነገገ ተግባሩ መሆኑን አ... | የመንግስት ባለስልጣናትን ሀብት በመጪው መስከረም ወር ለህዝብ በይፋ እንደሚያሳውቅ የፌደራል ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ናስታወቀ። |
መንግስት ሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለመጀመር ታሳቢ ካደረጋቸው መስፈርቶች መካከል አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት በነጠላ አሀዝ ውስጥ ይሆናል የሚል ቢሆንም፣ በሀምሌ ወር የጀመረው ባለሁለት አሀዝ የዋጋ ግሽበት በነሀሴ ወርም ነጥብ ስድስት በመቶ ማደጉ ተገለፀ። ማእከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣን ነሀሴ ሀያ ስምንት ቀን ሁለት ሺህ ሰባት አመተ ምህረት ያወጣው የነሀሴ ወር አገር አቀፍ የሸማቾች ዋጋ መመዘኛ ኢንዴክስ እንደሚያሳየው፣ የነሀሴ ወር አገር አቀፍ ጠቅላላ የችርቻሮ ዋጋ ኢንዴክስ ከሁለት ሺ... | የነሀሴ ወር የዋጋ ግሽበት ነጥብ ስድስት በመቶ ማደጉን ስታትስቲክስ ባለስልጣን አስታወቀ |
አዲስ አመት ደመና ጭጋጉ ሲገፍለት በተራው ሲፈካ ሰማይ ምድሪቱ በቀለማት ህብር ስትደምቅ ስትሞሸር ባደይ አትምጪ ይቅርብሽ ከኔ አትምጪ ነገን ሰንቀሽ እሰይ መስከረም ጠባ አዲስ ቀን ነው ብለሽ ይልቁን የውስጤ ዝናብ ሲያባራ የመንፈሴ ሰማይ ሲጠራ የልቤ አደይ ሲፈካ የተስፋ ፀሀዬ ስትበራ ያኔ ነይልኝ በሰኔ ነይልኝ ባምሌ ነሀሴው ነይልኝ ለእንቁጣጣሽ አዲስ ቀን አዲስ አመት ነው። ታዬ አስፋው፣ ሀጢሾ ሁለት ሺህ ስምንት መኖሪያ ቤት ውስጥ የገባው ፔንጉዊን በቁጥጥ... | የዘንድሮው የመስቀል በአል ደመራ መስከረም ቀን ሁለት ሺህ ዘጠኝ አመተ ምህረት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሲከበር |
ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር በማእከላዊ ጎንደር ዞን በላይ አርማጭሆ ወረዳ እየተከናወኑ ያሉ የችግኝ ዝግጅትና የተፋሰስ ልማትን እየጎበኙ ነው።ባህር ዳር፡ ጥር አራት ሁለት ሺህ አመተ ምህረት አብመድ ርእሰ መስተዳድሩ በወረዳው በሹማራ ሎምየ ቀበሌ የባንብላ ተፋሰስ ልማትን ተመልክተዋል።ባለፉት አመታት በተከናወነው የተፋሰስስ ልማት ስራ ቡና፣ ማንጎ፣ ሙዝ፣ጌሾና ሌሎች ገበያ ተኮር አትክልትና ፍራፍሬ በአካባቢው አርሶ አደሮች እየለማ ይገኛል።አርሶ አደር ተስፋ ሀይሌና ብርሀን ፈንቅለው እንዳሉት እነርሱን ... | ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር በማእከላዊ ጎንደር ዞን በላይ አርማጭሆ ወረዳ እየተከናወኑ ያሉ የችግኝ ዝግጅትና የተፋሰስ ልማትን እየጎበኙ ነው። |
የታገቱ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን አጠቃላይ ዝርዝር ሁኔታ የሚያሳይ መረጃ በቅረቡ ለህዝቡ ይፋ እንደሚደረግ የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።በደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ግጭት መከሰቱን ተከትሎ ወደ ቤተሰቦቻቸው በመሄድ ላይ የነበሩ ተማሪዎች መታገታቸው ይታወሳል። እነዚህን ተማሪዎች ያሉበትን ሁኔታ የሚገመግም በፌዴራል ደረጃ በጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ እየሰራ እንደሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሀላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ከአሀዱ ቲቬ ጋር በነበራቸው ... | መንግስት በደምቢ ዶሎ በታገቱ ተማሪዎች ዙሪያ የደረሰበትን መረጃ በቅርቡ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ገለፀ። |
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና በማረጋገጥ ረገድ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት መሆኑን የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ገለፁ። የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ይፋዊ የማብሰሪያና ክልሉን የማስተዋወቂያ መርሀ ግብር በሆሳእና ከተማ ተካሂዷል። የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ባስተላለፉት መልእክት፥ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና በማረጋገጥ ረገድ ትልቅ ተስፋ የተጣለ... | የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና በማረጋገጥ ረገድ ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ነው አቶ አደም ፋራህ |
ሯንዳ እና ህንድ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን የበለጠ ማጠናከር የሚያስችላቸውን ሰባት ማእቀፎች ላይ ተስማሙ።ስምምነቶቹ የመከላከያ፤ የንግድ እና የባህል ልውውጦችን እንደሚያካትቱ ለማወቅ ተችሏል።ሯንዳ እና ህንድ ከዚህ ቀደም የነበራቸውን ትብብር የበለጠ ለማተናከር ያስችላል የተባሉ ሰባት ጉዳዮች ላይ ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል።የሯንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ እና የህንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ በሯንዳ ኡርግዊሮ መንደር ነው ስምምነቱን የተፈራረሙት።ጠቅላይ ሚንስትር ሞዲ ለሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት... | ሯንዳና ህንድ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ |
ቤልጂየማዊው ኢንተርናሽናል አድናን ያንዩዣይ የዘንድሮ ሲዝን የጀመረው ለማንቸስተር ዩናይትድ ጎል በማስቆጠር የታጀበ ጥሩ እንቅስቃሴን በማሳየት ቢሆንም በሆላንዳዊው አሰልጣኝ ሉዊ ቫንሀል ግን ከፒ ኤስ ቪ አይንደንሆቨን የገዙት ሜምፌስ ዴፓይን ውጤታማ ፉትቦልን ለማጉላት በመጓጓት ያንዩዣይን በውሰት ውል ወደ ቦሪሽያ ዶርትሙንዱ የመልቀቅ ውሳኔ ላይ ደርሰዋል። ያንን ውሳኔያቸውን በማስመልከት ቫንሀል በተደጋጋሚ በሰጡት መግለጫዎች ከጀርመን ቡንደስሊጋ ውድድር በመሳተፍ በቂ ልምድን አግኝቶ እንደሚመለስልኝ በመጓጓ... | የአድናን ያንዩዣይ መመለስ ለማንቸስተር ዩናይትድ የሚያስገኙለት ቁልፍ ጠቀሜታዎች |
በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች አሸንፈናል ተቃዋሚዎች ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የከተማ ምክር ቤቶች ምርጫ ኢህአዴግ ጊዜያዊ ውጤት በመጥቀስ በሁሉም ቦታዎች እንዳሸነፈ የገለፀ ሲሆን በምርጫው የተሳተፉ ተቃዋሚዎች በውጤቱ እርግጠኛ ባይሆኑም በጥቂት የአዲስ አበባ ምክር ቤት ቦታዎች የምናሸንፍ ይመስለናል ብለዋል። የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ አየለ ጫሚሶ ህዝቡ ጥሩ ድምፅ እንደሰጠን እናውቃለን። ውጤቱን በተመለከተ ግን የምርጫ ቦርድ ይፋ ካደረገ በኋላ የምናየው ይሆናል ብለዋል። አቶ ... | ኢህአዴግ በሁሉም የምርጫ ቦታ አሸንፌያለሁ ይላል |
ለወትሮው ሁለቱ ቡድኖች በሚገናኙበት ጨዋታ ከፍተኛ ተመልካች ፣ ውጥረት እና የማሸነፍ ፍላጎት የሚኖር ሲሆን ዛሬ በይርጋለም ሁለገብ ስታድየም የታየውም ይኸው ነበር።የሲዳማ ቡና ደጋፊዎች ቡድናቸውን ለመደገፍ ወደ ስቴዲዮሙ መትመም የጀመሩት ገና ከማለዳ ጀምሮ ነበር ። ቁጥራቸው ጥቂት የማይባል የወላይታ ድቻ ደጋፊዎችም ክለባቸውን ለመደገፍ በስቴዲዮም ታድመው ነበር።የእለቱ አልቢትር ፌደራል ዳኛ ዳዊት አሳምነው የጨዋታውን መጀመር የፊሽካቸው ድምፅ ካሰሙበት ሰአት አንስቶ በመጀመርያዎቹ ደቂቃዎች ሲዳማ ቡና ከፍ... | የጨዋታ ሪፖርት የደቡብ ደርቢ በሲዳማ ቡና አሸናፊነት ተጠናቀቀ |
አዲስ አበባ፣ ሰኔ ስምንት፣ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ኢትዮ ቴሌኮም የአድቫንስድ አራትጂ ኤል ቲ ኤል አገልግሎት በደቡብ ምእራብ ሪጅን አስጀምሯል። ኢትዮ ቴሌኮም በአገልግሎቱ ጅማ፣ አጋሮ፣ በደሌ፣ ቦንጋ፣ ኮይሻ፣ መቱ፣ ማሻ ፣ ሚዛንና ቴፒ ከተሞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጿል። ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ምእራብ ሪጅን የሚሰጠዉን የኤል ቲ ኢ ዘመናዊ አገልግሎት በጅማ ከተማ የምረቃ መርሀ ግብር አስጀምሯል። በምረቃ መርሀ ግብሩ የኢትዮ ቴሌኮም ስራ አስፈፃሚ ቴሌብርን በተመለከተ ለተሳታፊዎች ገለፃ ያደረጉ ... | ኢትዮ ቴሌኮም የአድቫንስድ አራትጂ ኤል ቲ ኢ አገልግሎት በደቡብ ምእራብ ሪጅን አስጀመረ |
የኦሮሚያና አማራ ክልሎችን መጎብኘት አልቻለም በኢትዮጵያ ጉብኝነት ያደረጉት የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ዘይድ ራኢድ፤ በሀገሪቱ የሰብአዊ መብት ይዞታ ላይ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር የተወያዩ ሲሆን በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የታሰሩ የተቀዋሚ ፓርቲ አመራሮችንም ማነጋገራቸው ተጠቁሟል።ኤዴፓ፣ ሰማያዊና መኢአድን ጨምሮ የኢህአዴግ ተወካይ ባሉበት ከ ፓርቲዎች ጋር የተወያዩት ኮሚሽነሩ፤ በሀገሪቱ የሰብአዊ መብት አጠባበቅ፣ በሙስና እና በሚዲያ ነፃነት ጉዳይ ላይ የቀረበላቸውን አቤቱታ ካ... | የተመድ የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የታሰሩ የፓርቲ አመራሮችን አነጋግረዋል |
አዲስ አበባ፣ ጥር ስላሳ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ አምስትኛው የብስክሌተኞችና የእግረኞች ቀን በመላዉ የሀገሪቱ ከተሞች ተከበረ። የትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ኢንጂነር የኋላሸት ጀመረ በአዲስ አበባ ከቤቴል ሚካኤል አንፎ ስላሴ በተካሄደዉ መርሀ ግብር ተገኝተው እንዳሉት የትራፊክ አደጋን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የእግር ጉዞና የብስክሌት ትራንስፖርትን ለማበረታታት ከጳጕሜን እስከ ጳጉሜን እንደርሳለን በሚል መሪ ሀሳብ የተጀመረውን ንቅናቄ በማስቀጠል ዛሬ ለአምስትተኛ ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ በ... | አምስትኛው የብስክሌተኞችና የእግረኞች ቀን ተከበረ |
እንዴት ሰነበታችሁሳ ሀሳብ አለን ነገሮች መለዋወጣቸው ካልቀረ ለ አራድነት ደረጃ ይውጣልን። ተቸገርን እኮ እኔ የምለው አለ አይደል የ አራድነት የሶስት ወር ስልጠና ምናምን ተጀመረ እንዴ እንደዛ ከሆነ እውቅና የሌላቸው አሰልጣኞች በዝተዋል ማለት ነው ቂ ቂ ቂ እኔ የምለው እነ እንትና የዘንድሮው አራድነት እናንተን አይመለከትም። አሀ እንዴት ብሎ ደረጃ ይውጣ በምን መለኪያ አስር ብር በሚመስሉ የሎተሪ ትኬቶች ዶሮ ማነቂያን ያመሳችሁት እኮ ዘንድሮ አራድነት ሳይሆን ህገ ወጥ የምናምን ዝውውር አይነት ነው። ... | ቢያገኝም ያበላል ቢያጣም ያዝናል ሆዱ |
በአሰፋ አደፍርስ አገሬ ኢትዮጵያ ማን ይሆን ወገንሽ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ ሲበላሽ፣ ታዛቢ ያጣሽ ወገን የራቀሽ፣ መከራና ችጋር ተታውሮሽ ደረስኩልሽ የሚል ወገን ያጣሽ፣ ... | ፍቅርና ጥላቻ ሁሌም ቢፎካከሩ ማነው አሸናፊው |
አፕል በአይፎን ዋጋ ላይ ቅናሽ ሊያደርግ እንደሚችል ተነግሯል ላለፉት ተከታታይ አመታት በአለማቀፉ የስማርት ፎን ገበያ ከፍተኛውን ድርሻ ይዞ የዘለቀው የደቡብ ኮርያው ሳምሰንግ፤ ያለፈውን የፈረንጆች አመት ሁለት ሺህ በቀዳሚነት ማጠናቀቁን ካናሊስ የተባለው የስማርት ፎን ገበያ የጥናት ተቋም አስታውቋል።ካናሊስ ከሰሞኑ ይፋ ባደረገው ሪፖርት እንዳለው፤ በሁለት ሺህ የፈረንጆች አመት አለማቀፍ የስማርት ፎን ገበያ ውስጥ የሀያ አንድ ነጥብ ሁለት በመቶ ድርሻ የያዘው ሳምሰንግ በአመቱ ሁለት መቶ ዘጠና ሶስት ... | ሳምሰንግ በአለማቀፉ የስማርት ፎን ገበያ ክብሩን አስጠብቋል |
አዲስ አበባ፣ መጋቢት ሀያ ስድስት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ ህዝቡ ያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ የተደራጀ እቅድ በማዘጋጀት ወደ ስራ መገባቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርእሰ መስተዳደር አሻድሊ ሀሰን ገለፁ። ርእሰ መስተዳድሩ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ፥ ህዝብ ምላሽ ሊሰጥባቸው ይገባል በሚል የሚያነሳቸው ጥያቄዎች ተለይተዋል። በዚህም የሰላም፣ የኑሮ ውድነት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም ህገወጥ የማእድን ንግድን የመሳሰሉት ጉዳዮች ምላሽ እንዲሰጥባቸው ህዝቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎ... | ህዝቡ ያነሳቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ እቅድ በማዘጋጀት ወደ ስራ ተገብቷል አቶ አሻድሊ ሀሰን |
ጥር አስራ ስምንት ቀን አመተ ምህረትኢሳት ዜናኢሳት ያነጋገራቸው ደጋፊዎች እንዳሉትምንም እንኳ ብሄራዊ ቡድኑ ከቡርኪና ፋሶ ጋር በተጫወተበት እለት ያገኘው ውጤት አሳዛኝ ቢሆንም በቀጣዩ ጨዋታ የናይጀሪያን ቡድን በማሸነፍ ለቀጣዩ ዙር ለማለፍ ድጋፋቸውን አጠንከረው እንደሚሰጡ ገልፀዋል።በደቡብ አፍሪካ የሚኖረው ደጀኑ በቀለ ድሉ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚሆን ሙሉ እምነት እንዳለው ገልጿልከቡርኪና ፋሶ ከነበረው ጨዋታ በፊት ኢትዮጵያውያን ኮከብ ካለው ሰንደቃላማዎች ውጭ ሌሎችን ሰንደቃላማዎችን ይዘው ወደ ሜደ እ... | በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከዋሊያዎች ጎን እስከመጨረሻው እንደሚቆሙ ገለፁ |
ባህር ዳር፡ ግንቦት ሁለት ሁለት ሺህ አመተ ምህረት አብመድ በጆን ሆፒኪንስ ዩኒቨርሰቲ መረጃ መሰረት በአለማቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአራት ሚሊዮን አንድ መቶ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ አልፏል። የሟቾች ቁጥርም ከሁለት መቶ ሰማኒያ ሺህ በላይ ደርሷል። ከዚህ ውስጥ አሜሪካ በቫይረሱ ከተያዙት ከሩብ በላዩን፣ ከሞቱት ደግሞ ሲሶውን ድርሻ ትወስዳች።ባለሙያዎች ታዲያ የሀገራት የመመርመር አቅም ውስን መሆን እንጅ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከምንሰማው በጣም ከፍ ያለ ነው እያሉ መሆኑን ቢቢ... | በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአራት ሚሊዮን መብለጡ ቢገለፅም ከዚያም በላይ እንደሆነ ተመላከተ። |
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዘርአይ አስገዶምን ዘረኛና ጎጠኛ ሲሉ የፓርላማ አባላት አወገዙ። አባላቱ ኢህአዴግን ተጠልሎ ዘረኝነትን በኦፊሴላዊ ደረጃ ማራመድ፣ስልጣንን ማሳነስና የስም ማጥፋት ዘመቻ መክፈት ተጠያቂ ያደርጋል ብለዋል። የኮሚኒኬሽን ፅህፈት ቤትም ሆነ ሚኒስትሩ የሚወክሉት መንግስትን የሚያንፀባርቁትም የመንግስትን አቋም ነው ብለዋል አባላቱ። የመንግስት ኮሚኒኬሽኝ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ህዳር ሁለት ሺህ አስር ለፓርላማው የባህል፣ ቱሪዝምና መገናኛ ብዙሀን ጉዳዮች ቋሚ ኮ... | ዘርአይ አስገዶምን ዘረኛና ጎጠኛ ሲሉ የፓርላማ አባላት አወገዙ |
አርባ ሰባት ፒተር ኗዲኬተጠናቀቀ ጨዋታው በኤሌክትሪክ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ኤሌክትሪክም ከመውረድ ተርፏል።የተጫዋች ለውጥ ኤሌክትሪክ ዘጠና ሁለት ፍፁም ገብረማርያም ወጥቶ ተስፋዬ መላኩ ገብቷል።ተጠማሪ ደቂቃ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ አራት ደቂቃ ተጨምሯል። ኤሌክትሪክ በሊጉ መቆየቱን ለማረጋገጥ እጅግ ተቃርቧል። አወት ከርቀት የሞከረው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቷል። ዳኛቸው በቀለ ወጥቶ ሰለሞን ገብረመድህን ገብቷል። ብሩክ አየለ ወጥቶ ማናዬ ፋንቱ ገብቷል። ኤፍሬም አሻሞ ወጥቶ አምሀ በለጠ ገብ... | ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት |
የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ሪፖብሊካን ፕሬዚዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ባለፈው ሳምንት በተከናወነው ምርጫ ማሸነፋቸው ለተነገረላቸው ለዲሞክራቱ ጆ ባይደን የእንኳን ደስ ያለዎ መልእክት አስተላልፈዋል። ተመራጩ ፕሬዚዳንት ሀገራችንን የመምራት እና አንድ የማድረግ እድል አሸናፊ ሆነዋል ብለዋል ጆርጅ ቡሽ።እአአ ከሁለት ሺህ አንድ እስከ ሁለት ሺህ ዘጠኝ ሀገሪቱን የመሩት ቡሽ ከባይደን ጋር የፖለቲካ ልዩነቶች አሉን፤ የሆነ ሆኖ በስራቸው ስኬት እንዲያገኙ እፀልይላቸዋለሁ። በምችለው ሁሉ ልረዳቸው ቃል እገባለሁ ብለ... | ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ለጆ ባይደን የእንኳን ደስ ያለዎ መልእክት አስተላለፉ |
ቤተመፃህፍት ለመክፈት አቅዷል በዱከም ከተማ ተወልዶ ያደገውና የቴኳንዶ መምህር ወጣት ኤርሚያስ አሻግሬ ግለሰቦችና ተቋማት ማንኛውንም አይነት መፅሀፍት እንዲለግሱት ጠየቀ። በከተማዋ ለወጣቶች የተመቻቸ የመዝናኛም ሆነ የማንበቢያ ቦታ ባለመኖሩ ወጣቶች ለአጉል ባህርያትና ለሱስ መጋለጣቸውን የጠቆመው ወጣት ኤርምያስ ለመታደግ ቤተ መፅሀፍት ለመክፈት ከራሱና በቅርብ ከሚያውቃቸው ወዳጅ ጓደኞቹ መፃህፍቱ ማሰባሰብ መጀመሩን ገልፆ እስካሁን ወደ ያህል የተለያየ ይዘት ያላቸው መፅሀፍት ማግኘቱን አስታውቋል። ጉዳዩን ... | የዱከሙ ወጣት የመፃህፍት ልገሳ እየጠየቀ ነው |
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ ሰባት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በቀጣይ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት እንደሚሰራ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለፁ። የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት የሁለት ሺህ በጀት አመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ በሆሳእና ከተማ እየተካሄደ ነው። አቶ እንዳሻው በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር ያለፉት ዘጠኝ ወራት ለአጠቃላይ ተግባራት መሳካት መደላድል የተፈጠረበት እና አመራሩን በ... | አቶ እንዳሻው ጣሰው የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ገለፁ |
አዲስ አበባ፣ የካቲት ስምንት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በሱዳን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ይበልጣል አእምሮ በሱዳን ከሩሲያ አምባሳደር ቭላድሚር ዜልቶቭ እና ከስዊዘርላንድ አምባሳደር ክርስቲያን ዊንተር ጋር ተወያዩ። አምባሳደሩ በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ፣ በኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይ ላይ ገለፃ አድርገዋል። እንዲሁም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ዙሪያ ተወያይተዋል። በውይይቱም አምባሳደር ይበልጣል በተጠቀሱት ጉዳዮች ዙሪያ መንግስት ያለውን አቋም አስረድተዋል። የሩሲያው... | አምባሳደር ይበልጣል አእምሮ በሱዳን ከሩሲያ እና ስዊዘርላንድ አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ |
ጠቅላይ አቃቤ ህግ በማካይድራ የሰዎች ግድያ ላይ የተሳተፉ ሁለት መቶ ሰባ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን ከተሰበሰቡ መረጃዎች መረዳት እንደቻለ ገለፀ። አቃቤ ህግ በትናንትናው እለት ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመሆን መግለጫ የሰጠ ሲሆን ከተጠርጣሪዎች መካከልም ስላሳ ስድስትቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቋል። በጠቅላይ አቃቤ ህግ የሙስና እና የተደራጁ ወንጀል ጉዳዮች ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አቶ ፍቃዱ ፀጋ እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል እና የወንጀል ምርመራ ቢሮ ሀላፊ ዘላለም መን... | ትግራይ፡ በማይካድራ ግድያ ከተጠረጠሩት መካከል ስላሳ ስድስትቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ |
አዲስ አበባ፣ የካቲት አምስት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የሶማሌ ማይክሮ ፋይናንስ ወደ ሸበሌ ባንክነት ተሸጋግሯል። ማይክሮ ፋይናንስ ተቋሙን ወደ ባንክ የማሳደጊያ መርሀግብሩ በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው። በመርሀ ግብሩ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል። በሁለት ሺህ ሶስት የተመሰረተው ብድር እና ቁጠባ ተቋሙ፣ ሄሎ ካሽ በተሰኘ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት በስፋት ይታወቃል። የሸበሌ ባንክ አሁን ላይ ከግማሽ ቢሊየን ብር... | የሶማሌ ማይክሮ ፋይናንስ ወደ ባንክነት ተሸጋገረ |
በመካከለኛው ምስራቅ በፐርሺያን ገልፍ ሰሜን ምእራብ ጫፍ የምትገኝ በረሀማ ነገርግን ስትራቴጂካዊ እና በነዳጅ ሀብት የበለፀገች አገር ናት። ለዜጎቿም ሆነ ለሌሎች አገሮች ዜጎች በነፃ ህክምና ትሰጣለች። የአገሪቱ ዜጎች ከመንግስታቸው ሌሎች የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን ያገኛሉ። የኩዌት ዲናር አቅም ካላቸው ገንዘቦች በቀዳሚነት የሚመደብ ሲሆን አንዱ ዲናር ሶስት ብር ከሀምሳ የአሜሪካን ዶላር ይመነዘራል። ኩዌት በህገመንግስታዊ የንጉስ ስርአት የምትመራ አገር ናት።ባለፈው ሳምንት ባዘጋጀችው ሶስተኛው የአፍሪካ አረብ... | የፍልሰት ጉዳይ መፍትሄ ካልተሰጠው የአፍሪካንና የአረቡን አለም ግንኙነት እስከማቋረጥ ሊደርስ ይችላል የኩዌት ፖለቲካ ተንታኝ |
አዲስ አበባ፣ ህዳር ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለኢትዮጵያ ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላለፉ። ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍሎ የመከላከያ ሀይላችን ላጎናፀፈን ክብር መላው ኢትዮጵያውያንን እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን ብለዋል። ህግ የማስከበሩ ምእራፍ በድል ተጠናቋል፤ በመጭው ጊዜ ደግሞ ትልቅ ስራ እንደሚጠብቀን ለአፍታም አንዘናጋ ነው ያሉት። እጅ ለእጅ ተያይዘን የሀገራችንን ልማትና እድገት ለማረጋገጥ ጠንክረን እንስራ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል። የ... | ህግ የማስከበሩ ምእራፍ በድል ተጠናቋል በመጭው ጊዜ ትልቅ ስራ እንደሚጠብቀን አንዘናጋ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ |
መረጃው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ነው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ከሀያ ስምንትኛ፣ ሀያ ዘጠኝኛ እና ስላሳኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሚየር ሊግ ውድድር መርሀ ግብር ጋር በተያያዘ በፌዴሬሽኑ ከህግ ውጪ ተወስኖብኛል ስላላቸው ቅጣቶች ልዩ ልዩ ሰነዶችን በአባሪነት በማያያዝ የይግባኝ አቤቱታ በይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ውስጥ አስፈላጊው ክፍያ ከተፈፀመበት ደረሰኝ ጋር አቅርቧል። የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴውም የቀረበለትን ጥያቄ በዝርዝር ተመልክቷል።የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ፣ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን... | የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔ በቅዱስ ጊዮርጊስ ይግባኝ ዙርያ |
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ሰባትኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገ እና እሁድ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይቀጥላል። በተቀራራቢ ደረጃ ላይ የሚገኙ ክለቦች የሚያደርጉት ፍልሚያም ይጠበቃል።የምድብ ሀ ሁሉም ጨዋታዎች እሁድ የሚደረጉ ሲሆን በአንድ ነጥብ ልዩነት በደረጃ ሰንጠረዡ ሁለትኛ እና ሶስትኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ፋሲል ከተማ እና መቀለ ከተማ ጎንደር ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ነው። በባህርዳር ደርቢ ባህርዳር ከተማ ከ አማራ ውሀ ስራ ማክሰኞ ሲጫወቱ መሪው አአ ፖሊስ ሱሉልታ ከተማን እሁድ ያስተናግዳል... | የከፍተኛ ሊግ ሰባትኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገ እና እሁድ ይደረጋሉ |
ኢትዮጵያን ከአንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀያ ስምንት እስከ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ስላሳ ሶስት አመተ ምህረት ድረስ ወርሮ የነበረው የኢጣሊያ ፋሺስት ሰራዊት፣ ድል የተመታበትን ሰባ አምስትኛ አመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ የድል በአል ምክንያት በማድረግ ሶስት የውጭ አገር ዜጎችን ጨምሮ ለሀያ አምስት ታላላቅ አርበኞች የመታሰቢያ ቴምብር ታተመላቸው። የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ሰባ አምስትኛ አመት መታሰቢያ የድል በአል በሚል ርእስ ያሳተመው ስድስት አይነት ቴምብሮችን ሀዳር አንድ ... | ለሀያ አምስት ታላላቅ አርበኞች የመታሰቢያ ቴምብሮች ታተሙ |
አዲስ አበባ፣ ሰኔ ሀያ ስምንት፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ አሜሪካ ለታይዋን የጦር መሳሪያዎችን ልትሸጥ አይገባም ስትል ቻይና በፅኑ ተቃውማለች። ባሳለፍነው መጋቢት ወር አሜሪካ የስድስት መቶ ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የጦር መሳሪያዎችን ለታይዋን ለመሸጥ ማፅደቋ ይታወሳል። የቻይና የመከላከያ ሚስቴር ቃል አቀባይ ታን ኬፌይ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አሜሪካ ከታይዋን ጋር ያላትን ወታደራዊ ግንኙነት በአስቸኳይ እንድታቋርጥ አሳስበዋል። የቻይና እና የታይዋን ጉዳይ የውስጥ ጉዳይ በመሆኑ አሜሪካ ጣልቃ ገብታ ውጥረቱን ከ... | ቻይና አሜሪካ ለታይዋን የጦር መሳሪያ እንዳትሸጥ ተቃወመች |
ክርስቲያን ኤይድ የተሰኘው በጎ አድራጎት ድርጅት ባወጣው ሪፖርት መሰረት አለማችን እየተጠናቀቀ ባለው የፈረንጆቹ አመት በከፋ የአየር ንብረት ለውጥ መመታቷን አስታወቀ። ድርጅቱ በሁለት ሺህ ሀያ የተከሰቱ እና በአለማችን ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ ያስከተሉ አስር ጉልህ ክስተቶችን መርጧል። ከእነዚህ መካከል ስድስቱ በእስያ የተከሰቱ ሲሆኑ በቻይናና በህንድ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ ከአርባ ቢሊዮን ዶላር በላይ ውድመት አስከትሏል ሲል ያትታል። በአሜሪካ የተከሰተው ከባድ አውሎ ንፋስ እና ሰደድ እሳት ደግሞ ... | በፈረንጆቹ ሁለት ሺህ ሀያ ከባድ የአየር ሁኔታ አለምን ለኪሳራ ዳርጓታል ተባለ |
ሪፖርተር መጋቢት አራት ቀን ሁለት ሺህ አምስት አመተ ምህረት የተቃውሞ ደብዳቤ ለፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ያቀረቡት የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች፣ ላለፉት አስር ቀናት ትምህርታቸውን ከማቆማቸውም በተጨማሪ፣ ከመጋቢት ቀን ሁለት ሺህ አምስት አመተ ምህረት ምሽት ጀምሮ የረሀብ አድማ ማድረጋቸው ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ታትሞ የወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገበ። እንደሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ ተማሪዎቹ ያቀረቡት የተቃውሞ ደብዳቤ ለአንድ ሳምንት ምላሽ ስለተነፈገው፣ መጋቢት ቀን ሁለት ... | የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ከትምህርት ማቆም አድማው በተጨማሪ የረሀብ አድማ ጀመሩ |
አዲስ አበባ፣ መስከረም ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በጋይንት እና አካባቢው የህውሀት የሽብር ቡድን በግፍ ለተረሸኑ እና ሀገራችን አናስደፍርም ብለው አንገት ለአንገት ተናንቀው ህይወታቸው ላጡ ቤተሰቦች በውጭ ሀገር በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ ተደርጓል። ድጋፉ ለተሰው፣ ለቆሰሉ እና ለተደፈሩ ሴት እህቶች እና እናቶቻችን መከታ ለወገን ከተሰኝ በውጭ ሀገር እና በሀገር ውስጥ ከሚገኙ ወገኖች የተሰበሰበ ገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል። የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀለምወርቅ ምህረቴ፥ የተሰው ወገኖች ለሀ... | በህወሀት የሽብር ቡድን በግፍ ለተረሸኑ መታሰቢያ እና ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ተደረገ |
በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ እየተመሩ በርካታ ዝውውሮችን ከፈፀሙ በኋላ ከነባሮቹ ጋር በማቀናጀት ያለፉትን ሳምንታት በሆሳእና ከተማ ቅድመ ዝግጅታቸውን እየሰሩ የሚገኙት ሀድያ ሆሳእናዎች ሁለት የውጪ ዜግነት ያላቸውን ተጫዋቾች ወደ ክለቡ አምጥተዋል።የመጀመሪያው ፈራሚ ከአራት አመታት በሀላ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው አይዛክ ኢሴንዴ ነው። የሀገሩን ክለብ ቪክቶርን ለቆ ከስድስት አመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በሀላ ቅዱስ ጊዮርጊስን በመቀላቀል በክለቡ አምስት አመታት አስደናቂ ብቃቱን ሲያሳይ እንደነበር ... | ሀድያ ሆሳእና ሁለት የውጪ ዜጋ ተከላካዮችን አስፈረመ |
በሀዳር ወር ሁለት ሺህ አመተ ምህረት ይካሄዳል ተብሎ ከታቀደው የደቡብ ክልል የሲዳማ ዞን ህዝበ ውሳኔ አስቀድሞ አስተዳደራዊና ህጋዊ ማእቀፎች በማዘጋጀት፣ እንዲሁም ተአማኒ በሆነ የጊዜ ሰሌዳ ላይ አስቀድሞ መግባባት ላይ በመድረስ ህዝበ ውሳኔውን ለማካሄድ የሚያስችል ምቹ የፖለቲካ ሁኔታ ለመፍጠር አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ዶክተር አሳሰቡ። ዋና ኮሚሽነሩ ይህን ማሳሰቢያ የሰጡት ከመስከረም ሰባት እስከ ዘጠኝ ቀን ሁለት ሺህ አመተ... | የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከሲዳማ ዞን ህዝበ ውሳኔ በፊት ምቹ የፖለቲካ ሁኔታ እንዲፈጠር አሳሰበ |
ከኢሳያስ ከበደ ላለፉት አመታት የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት በመሆን ከአበባ መቁረጥና መትከል ከእንግዳ መቀበልና መሸኘት በስተቀር አንዳችም ስልጣን ያልነበራቸውን ፕሬዚዳንት ግርማ ወጊዮርጊስን በመሸኘት አዲስ አበባ ቆራጭ ፕሬዚዳንት እንደሚመረጥ የኢህአዴግ ፓርላማ አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ አስታውቀዋል። እንደ አስተያየት ሰጪዎች ገለፃ ለፕሬዚዳንትነት የሚመረጠው ሰው ከፓርላማው ውጭ ያለም ሰው ሊሆን እንደሚችል የተገለፀ ሲሆን ፕሬዚዳንት የሚለው ስያሜ ከአበባ መቁረጥ ያለፈ ስልጣን ስለሌለው በርከት ያሉ ኢ... | የፊታችን ሰኞ የኢህአዴግ ፓርላማ አበባ ቆራጭ ይሾማል |
የካቲት ዘጠኝ ቀን ሁለት ሺህ አስር አመተ ምህረት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅና ተግባራዊ መሆን የሚገባቸውን ድንጋጌዎች ተላልፈዋል ተብለው በኮማንድ ፖስቱ ታስረው የከረሙት፣ የኦሮሚያ ክልል ልዩ አድማ በታኝ ፖሊስ ምክትል አዛዥ፣ የፍትህ ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን ሀላፊና የአምቦ ዩኒቨርሲቲ መምህር ከእስር ተፈቱ። በኮማንድ ፖስቱ ተጠርጥረው ላለፉት ስላሳ ዘጠኝ ቀናት በእስር ላይ የከረሙት ምክትል አዛዡ ኮማንደር ኢሳያስ አንጋሱ፣ የፍትህ ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን ሀላፊ አቶ ታዬ ደንዷ፣ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ወሊሶ ካምፓ... | በኮማንድ ፖስቱ ታስረው የነበሩ የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ ምክትል አዛዥና የፍትህ ቢሮ ቃል አቀባይ ተፈቱ |
አዲስ አበባ፡ በአገር አቀፍ ደረጃ ሁለት ጠንካራ ፓርቲ ብቻ እንዲኖር ፍላጎቱ አለኝ ሲሉ የቀድሞ የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ አስታወቁ።ኢህአዴግ ከእህት ድርጅቶቹና ከአጋር ድርጅቶች ጋር ውህደት ለማድረግ ማሰቡንም በአድናቆት ተመልክተውታል።አቶ ኦኬሎ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደተናገሩት፣ ኢህአዴግ ባለው ተመሳሳይ አቋም በውስጡ ያሉ እህት ድርጅቶቹን እንዲሁም አጋር ድርጅቶችን ይዞ ውህደት ቢፈጥር ፣ተፎካካሪ ፓርቲዎችም እንዲሁ ባላቸው ተመሳሳይ አቋም አንድ በመሆን በአገሪቱ ሁለት ጠንካራ ፓር... | በአገር አቀፍ ደረጃ እንዲኖር የምፈልገውሁለት ጠንካራ ፓርቲ ብቻ ነው አቶ ኦኬሎ አኳይ የቀድሞ የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት |
አዲስ አበባ፣ ህዳር አንድ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በትግራይ ክልል ህግ በማስከበር ዘመቻ ላይ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊትን እና ለሌሎች ፀጥታ አካላትን ለመደገፍ የገቢዎች ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች የደም ልገሳ እያደረጉ ይገኛል።ከሁለት መቶ በላይ የተቋሙ ሰራተኞች በበጎ ፍቃድ ደም የለገሱት በግዳጅ ላይ ለሚገኙ የፀጥታ አካላት ከጎናቸው መሆናቸውን ለማሳየት በማለም መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል።የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው እንደተናገሩት የሀገርን ሏላዊነት... | የገቢዎች ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች የደም ልገሳ አደረጉ |
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ተመራማሪ ትምኒት ገብሩ፣ በአለማችን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የምርምር መስክ እጅግ የላቀ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ ከሚገኙና በዘርፉ አስደናቂ ስኬት ካስመዘገቡ ድንቅ የአለማችን ሀያ አንድ ሴት ተመራማሪዎች አንዷ መሆኗን ታዋቂው ፎርብስ መፅሄት ዘግቧል።በልጅነቷ ወደ አሜሪካ ያመራቺው ትምኒት ገብሩ፣ የግልም ሆነ የሙያ ተግዳሮቶቻቸውን አሸንፈው በአለማችን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የምርምር መስክና በኢንዱስትሪው ውስጥ አስደናቂ ተፅእኖ መፍጠር ከቻሉና በግምባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱ ተፅ... | ትምኒት ገብሩ ከአለማችን ድንቅ ሀያ አንድ ሴት ተመራማሪዎች አንዷ ሆናለች |
አለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት አይ ኤል ኦ ኢትዮጵያን የማህበራትን የመደራጀት ነፃነት ከገደቡ ቀንደኛ አምስት ሀገራት አንዶ መሆኖን አስታወቀ። ጄኔቫ የሚገኘው አለም አቀፉ የሰራተኞች ማህበር ዛሬ ይፋ ባደረገው ሪፖርት እንዳስታወቀው የመሰባሰብና የመደራጀት ነፃነት ካፈኑና አደገኛና ፍፁም የሆነ ገደብ የጣሉ ሲል ካወጣቸው ስላሳ ሁለት ሀገራት ውስጥ ኢትዮጵያ፣ ካምቦዲያ፣ ፊጂ፣ አርጀንቲናና ፔሩ በዋነኝነት አስቅቀምጦቸዋል። የአይ ኤል ኦ ሪፖርት እንዳመለከተው እነዚህ ሀገሮች ከአንድ እስከ ሰላሳ ሁለት በሚደ... | አይ ኤል ኦ ኢትዮጵያ የመደራጀት መብትን አግዳለች አለ |
ከሙሉቀን ገበየሁበአገራችን ኢትዮጵያ የአገር ሽማግሌዎች የተከበሩና ብሂል ምክራቸውም የተደመጠ ነው። ባህላችንም ታሪካችንም ይሆንኑ ነው የሚነግረን። በመሀበራዊ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በተወሰነ መልኩ ፖለቲካዊና የወንጀል ጉዳዮች ላይ የሚሰጡት ብይንና ምክር ሁሌም የተከበረና ህብረተሰቡም ሲያከብርው የኖረ ባህላዊ እሴት ነበር። የአገር ሽማግሌዎች ያካበቱት እውቀት ልምድና ብሂል ባሉበት ሀገር ታላቁ የእውቀት መፅህፍ ኢንስይክሎፒድያ ያህል ያደርጋቸዋል። ይህ ለምእተአመታትና ለሺ አምታት ህብረተሰቡን አሁን ከምናየው... | እስኪ የተማሩ የአገር ሽማግሌዎቻችንን እናድምጥ ከሙሉቀን ገበየሁ |
የበላይ ባለስልጣናት በፈፀሙት ወንጀል እኛ ዋጋ እየከፈልን ነው ባለፈው ሀምሌ ወር በተካሄደው የፀረ ሙስና ዘመቻና በተለያዩ ጊዜያት በልዩ ልዩ የሙስና ወንጀሎች ተከሰው ጉዳያቸው በፍቤት እየታየ የሚገኘው ተከሳሾች ፍትህ ይሰጠን የሚል አቤቱታቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀረቡ። ጉዳያቸው በፍቤት ቀጠሮ ላይ የሚገኘው እነዚህ የሙስና ወንጀል ተከሳሾች ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እንዲቀርብላቸው የላኩት የ እስረኞችን ፊርማ ያካተተ የአቤቱታ ደብዳቤ ሲሆን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲደርስ በፌደራል ማረሚ... | በሙስና ወንጀል ተከሰው በቀጠሮ ላይ የሚገኙ ከ በላይ ተከሳሾች ለጠቅላይ ሚኒስተር አቤቱታ አቀረቡ |
አዲስ አበባ ፣ የካቲት ስምንት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሀ ግብር ዋና አካል የሆነው የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ውጤታማነት ለማሻሻል ፣ ተወዳዳሪነታቸውን ለማጎልበት እና የአገልግሎቶት አሰጣጣቸውን ቀልጣፋ እንዲሆኑ ለመደገፍ ያተኮረ ለአምስት ቀናት የሚቆይ ውይይት ተጀመረ። በመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ስር በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ፣ በግብርና እና ግብርና መቀነበባር፣ በአምራች ኢንዱስትሪ እና ኢንጅነሪንግ፣ የንግድ እና የአገልግሎት ዘር... | የመንግስት የልማት ድርጅቶች የግማሽ አመት ስራ አፈፃፀም እየተገመገመ ነው |
ከአራት አመታት ቆይታ በኋላ ከመቐለ ሰባ እንደርታ ጋር የተለያየው አሌክስ ተሰማ ቀጣይ ማረፍያው በቅርቡ ይታወቃል።ባለፉት ሶስት አመታት በዋናው ሊግ ደረጃ በወጥነት ጥሩ ብቃት ካሳዩት የመሀል ተከላካዮች አንዱ የሆነው አሌክስ ተሰማ የዳሽን ቢራ መፍረስ ተከትሎ በወቅቱ የከፍተኛ ሊግ ተወዳዳሪ ለነበረው መቐለ በሁለት ሺህ ዘጠኝ ፈርሞ በዛው አመት ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንድያድግ ሚና የነበረው ሲሆን በሁለት ሺህ ቡድኑ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ሲያነሳም ትልቅ ሚና ከነበራቸው ተጫዋቾች አንዱ ነው።ተጫዋቹ ከ... | መቐለ ሰባ እንደርታ ከተከላካዩ ጋር ተለያይቷል |
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ የአመራሩን የተግባር አንድነት ለማጠናከር ሰፊ ጥረት መደረጉን የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ተናገሩ። የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እና የፓርቲ የሁለት ሺህ የመጀመሪያው ሩብ አመት አፈፈፃፀም ግምገማ በአዳማ ገልማ አባገዳ እየተካሄደ ነው። የፅህፈት ቤት ሀላፊው አቶ ፍቃዱ ተሰማ በአንዳንድ አመራሮች መካከል ወጥ የሆነ የአመለካከት ውስንነት መኖሩ ክልሉን ዋጋ እንዳስከፈለው ገልፀው፥ ይህንንም ለማስተካከል ሰፊ ጥረት ተደር... | የአመራሩን የተግባር አንድነት ለማጠናከር ሰፊ ጥረት ማድረጉን የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ገለፀ |
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተመድ የምእተ አመቱን የልማት ግብ አጠናቆ፣ በሁለት ሺህ ስምንት አመተ ምህረት ተግባራዊ ማድረግ በጀመረው የ አመቱ የዘላቂ ልማት ግብ ተሳታፊ የሆነው የኢትዮጵያ መንግስት ፈቃደኛ በመሆን የአንድ አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርቱን ሊያስገመግም ነው። ኢትዮጵያን ጨምሮ አርባ አራት አገሮች የእቅድ አፈፃፀማቸውን ለማስገምገም ፈቃደኛ ሆነዋል።ብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ለተመድ በሚቀርበው የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከፌዴራልና ከክልል ባለሙያዎች ጋር እየመከረ ነው። እ ኤ አ በሁለት ሺህ ... | ኢትዮጵያ ለተመድ በፈቃደኝነት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ልታቀርብ ነው |
በቶፊቅ ተማምምንም የማይሰማ የማያይ እንዲሁም የማይናገር ሰው መቶ አመታትን በሰላም መኖር ይችላል። ይህ አባባል ኦሜርታ ተብሎ የሚጠራውን የዝምታ ህግ አስፈላጊነት ለመግለፅ በተለይ በጣሊያን ሲሲሊዎች ዘንድ የሚነገር የዘወትር ቃል ነው።ዛሬም ድረስ ታዲያ በአንዲት አገርና ህዝብ ላይ የፍርሀት ድባብ ሲነግስና የፍርሀቱም ምክንያት ከቡድን ወይም ከመንግስት አስተዳደር ጋር ሲገናኝ በውጤቱም ህዝብ እንዲሁም ምሁራን አላየሁም አልሰማሁም አልናገርም የሚል ዝምታ ሲፈጠር ክስተቱ ኦሜርታ ይባላል።በእርግጥ በዚህ ፅሁፍ... | የአገሪቱ ምሁራን በኦሜርታና በሰጎን ፖለቲካ ጥላ ስር |
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት ስድስት፣ ቀ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በምርቶችና ሸቀጦች ላይ አለአግባብ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ እንደሚያስፈልግ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገለፁ።ሚኒስትሩ ይህንን የገለፁት ከክልልና ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ሀላፊዎች ጋር መደበኛ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ውይይት ባካሄዱበት ውቅት ነው ተብሏል።ብዙ ጊዜ ለወቅታዊ የዋጋ ንረት ምክንያት የሚሆነው የንግድ ዘርፉ የመንግስት ተቋማት ቁጥጥር መለላት ነው ም ነው የተባለው።ስለሆነም ህብረተሰቡ... | በምርቶችና ሸቀጦች ላይ ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ ያስፈልጋል ተባለ |
በመላው አለም ከሁለት መቶ አገራት በላይ የተዛመተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የአለምን የስፖርት እንቅስ ቃሴ በከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ከቶታል። በወረርሽኙ ሳቢያ ትልልቅ የስፖርት ውድድሮች በመራዘማቸው፣ በመሰረዛቸው እና በመስተጓጐላቸው ኢንዱስትሪውን ከፍተኛ ገቢ እንደሚያሳጣው የተለያዩ ትንበያዎች አመልክተዋል። የስፖርት ኢንዱስትሪውን በስፖንሰ ርሺፕ የሚደግፉ ትልልቅ አለም አቀፍ ኩባንያዎች የበጀት ቀውስ ውስጥ መግባታቸው፣ ከትኬት ሽያጭ ከማርኬቲንግና ከተለያዩ ንግዶች የሚገኙ ገቢዎች መቆማቸው ሁሉንም ስፖር... | የፊፋ ድጎማ እግር ኳሱን ይታደገው ይሆን |
አለመግባባቱ ወጪና ገቢ እቃዎችን ለአጭር ጊዜም ቢሆን ሊያዘገይ ይችላል ተብሏል በጂቡቲ መንግስትና በዱባዩ የወደብ አስተዳዳሪ ኩባንያ ዲፒ ወርልድ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ሳቢያ፣ የጂቡቲ መንግስት ከኩባንያው ጋር የነበረውንና ለ አመታት የቆየ የወደብ አስተዳደር ስምምነት የጂቡቲ መንግስት ማቋረጡ የተሰማው ሀሙስ የካቲት ቀን ሁለት ሺህ አስር አመተ ምህረት ነበር። በሁለቱ ወገኖች አለመግባባት ሳቢያ በኢትዮጵያ ገቢና ወጪ እቃዎች ላይ ስጋት ሊፈጠር ይችል እንደሆነ ለኢትዮጵያ ማሪታይም ጉዳዮች ባለስል... | ጂቡቲ የዱባዩን የወደብ አስተዳዳሪ ኩባንያ ማሰናበቷ በኢትዮጵያ ላይ ስጋት ደቅኗል |
ሙዚቃን ለትግል በመጠቀም እና ለትግል በማነሳሳት ረገድ ሀጫሉ ሁንዴሳንና አሊ ቢራን የሚያመሳስላቸው ነገር አለ። በኦሮምኛ ሙዚቃ አዋቂዎችም ዘንድ ድምፃዊ ሀጫሉ የዚህ ዘመን አሊ ቢራ ነው፤ ለሚቀጥሉት አስርት አመታት ከአሊ ቢራ ተቀብሎ ወደሚቀጥለው ትውልድ የሚያስተላልፍ ነው ሲሉ ይገልፁታል። እነዚህ ሁለቱ ድምፃውያን ይተዋወቁ ነበር አሊ ቢራስ አርቲስት ሀጫሉን እንዴት ይገልፀዋል ለኔ ሀጫሉ የጀግኖች ጀግና ነው፤ የምንኮራበት ነው። በማለት አሊ ይናገራል። መጀመሪያ እነዚህ ሁለት ሰዎች፣ አሊ ቢራና ሀጫሉ፣ ... | ድምፃዊ አሊ ቢራ ስለ ሀጫሉ ሁንዴሳ ምን ይላል |
ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ አምስት ዘነብ ወርቅ ታቦት ማደሪያ አካባቢ፣ ጤፍን ከጀሶ ጋር በመቀላቀል እንጀራ ጋግረው ለጠቃሚዎች ያሰራጩ ግለሰቦች በአስር አመት ፅኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ። ድርጊቱን የፈፀሙት ተከሳሾቹ አንደኛ አልማዝ ሺፈሬና ሁለተኛ ጥሩሴት ወዲያ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሀምሌ ቀን ሁለት ሺህ ስምንት አመተ ምህረት ጤፍን ከጀሶ ጋር ቀላቅለው በመጋገር ላይ እያሉ ነበር። ተከሳሾቹ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት ሊጋገር የተዘጋጀ በተለያዩ እቃዎች ተቦክቶ የተቀመጠ የጤፍና የጀሶ ድብልቅ ... | ጤፍን ከጀሶ ጋር በመቀላቀል እንጀራ ጋግረው ያሰራጩ ግለሰቦች ተቀጡ |
ዋዜማ ራዲዮ የታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሀይሌ ገብረስላሴ ንብረት የሆነ ሪዞርት በአስቸኳያ ጊዜ አዋጁ ስበብ በኮማንድ ፖስቱ እንዲዘጋ መደረጉን የዋዜማ ሪፖርተሮች አረጋግጠዋል።በኦሮምያ ክልል ሱሉልታ ከተማ የሚገኘውያያ ሪዞርት ባለፈው ሳምንት የተጠራውን የሶስት ቀናት የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ አገልግሎት በማቋረጡ ሳቢያ የኮማንድ ፖስቱ ተቆጣጣሪዎች እንዳሸጉትና እስከ ቅዳሜ ምሽት ድረስ ተዘግቶ እንደነበር ተመልክተናል።ድርጅቱን ለማስከፈት አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እያደ... | የሀይሌ ገብረስላሴ የንግድ ተቋም በኮማንድ ፖስቱ ትእዛዝ ተዘጋ |
በደርግ ዘመነ መንግስት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትር የነበሩት ኮል ጎሹ ወልዴ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመንና እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ነብያት ጌታቸውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች አቀባበል አድርግውላቸዋል።የቀድሞው ሚኒስትር በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የደርግን አገዛዝ በመቃወም ሀላፊነታቸውን በፈቃዳቸው ከለቀቁና ኑሯቸውን በአሜሪካ ካደረጉ ... | ኮል ጎሹ ወልዴ አዲስ አበባ ገቡ |
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በክረምት የበጎ አድራጎት ስራ የማህበረሰቡን ችግር ለመቅረፍ እኔ ለወገኔ ጥላ እሆናለሁ በሚል መሪ ቃል እንደ ክልል በአንድ ቀን የአንድሺህ አንድ መቶ የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ስራ እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ። የኦሮሚያ የእቅድና የኢኮኖሚ ልማት ኮሚሽነር ዶክተር ተሾመ አዱኛ በዛሬው እለት በጅማ ዞን ዴዶ ወረዳ ተገኝተዉ የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት አስጀምረዋል። በዚሁ ወቅት በተለያዩ ምክንያቶች አቅም አንሷቸው መኖሪያ ቤታቸው ዘሞ ያስቸገራቸውን ... | ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር የበጎ አድራጎት ስራ ከፍተኛ ድርሻ አለዉ የኦሮሚያ የእቅድና የኢኮኖሚ ልማት ኮሚሽን |
አዲስ አበባ፣ መስከረም ዘጠኝ፣ ሁለት ሺህ ኤፍ ቢ ሲ በመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ስር ያሉ ዘጠኝ የልማት ድርጅቶች ከታክስ በፊት የስምንት ነጥብ ሁለት ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘታቸው ተገለፀ። በተጠናቀቀው የሁለት ሺህ በጀት አመት በአስተዳደሩ ስር ካሉት የልማት ድርጅቶች በአጠቃላይ አርባ አምስት ነጥብ ሶስት ቢሊየን ብር ጠቅላላ ገቢ መገኘቱንም ኢዜአ ዘግቧል። ገቢው ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የሀያ ሰባት በመቶ ብልጫ እንዳለው ተጠቁሟል። ድርጅቶቹ ለተለያዩ የሀብረተሰብ ክፍሎች ስድ... | ዘጠኝ የልማት ድርጅቶች ስምንት ነጥብ ሁለት ቢሊየን ብር ትርፍ ማግኘታቸው ተነገረ |
ከኡመልኸይር ቡሎ ካዪላ ዊህለር የተወለደችው ሁለት እግርና አንድ እጅ ሳይኖራት ነው። ሀኪሟም ዋናን እንደ አንድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንድትጠቀም ይመክራት ነበር። በእዚህ መሰረት ባደረገችው ጥረት ዊህለር ግን በ አመቷ በዋና የአለምን ሪከርድ ለመስበር ችላለች። ሲ ኤን ኤን እንደዘገበው ታዳጊዋ በብራዚል ሜክሲኮና ኔዘርላንድ ውድድሯን ያደረገች ሲሆን፤ በሁለት ሺህ ፓራኦሎምፒክ ለመወዳደር እቅድ ይዛለች። በሁለት ሺህ በተካሄደውሀምሳ ሜትር የሴቶች ሻምፒዮን ተወዳድራ አዲስ ሪኮርድ አስመዝግባለች። ነገሩን... | ሁለት እግርና አንድ እጅ አልባዋ የዋና ሻምፒዮን |
የአዲስ አበባና የአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን በገጠመው ተቃውሞ ከተሰረዘ በኋላ፣ የፌዴራል መንግስት በመላ አገሪቱ የተቀናጀ የከተማ ፕላን ለመፍጠር ያረቀቀው አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ። ረቂቁ በስራ ላይ የሚገኘውን የከተማ ፕላን አዋጅ ቁጥር አምስት መቶ ሰባ አራት ሁለት ሺህ ሙሉ በሙሉ የሚተካ ሲሆን፣ አላማውም በስራ ላይ ያለው አዋጅ ላይ የታዩ የአፈፃፀም ችግሮችን መቅረፍ ስለመሆኑ የረቂቁ ማብራሪያ ይገልፃል። አጠቃላይ አላማውም ከአገሪቱ ፖሊሲና የእድገት አቅጣጫ ጋር ... | ክልሎችን ከአጎራባች ክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች የሚያቀናጅ አገር አቀፍ የከተማ ፕላን ሊዘጋጅ ነው |
ከአንድ መቶ ስልሳ ሁለት መንገደኞች እስካሁን የሰባትቱ አስከሬን ተገኝቷልባለፈው እሁድ አንድ መቶ ስልሳ ሁለት ሰዎችን ይዞ በበረራ ቁጥር ስምንት ሺህ አምስት መቶ አንድ ከኢንዶኔዥያዋ ሱራያባ ከተማ ወደ ሲንጋፖር በመጓዝ ላይ እያለ ድንገት የተሰወረው ንብረትነቱ የኤርኤዥያ አየርመንገድ የሆነው ኤርባስ ኤሶስት መቶ ሀያ ሁለት መቶ አውሮፕላን እጣ ፋንታ አለምን አሳዝኗል። ኢንዶኔዢያውያንም አዲሱን የፈረንጆች አመት በጥልቅ ሀዘንና በአስከሬን ፍለጋ ተቀብለውታል።አውሮፕላኑን መሰወሩን ተከትሎ ኢንዶኔዢያና ሌሎች... | ኢንዶኔዢያውያን አዲሱን አመት በሀዘን ተቀብለውታል |
Subsets and Splits
No community queries yet
The top public SQL queries from the community will appear here once available.